Mittwoch, 10. Juni 2015

የምንመገበውን የስኳር መጠን መቀነስ ለምን ያስፈልጋል?

✓ የሰውነት ክብደትን ለመቀነስ
በብዛት ጣፋጭ ምግቦችን መመገብ ለሰውነት ክብደት መጨመር ዋነኛ ምክንያቶች ውስጥ አንደኛው ሲሆን ፍሩክቶስ የስብ ክምችት እንዲኖር ስለሚያደርግ እና ጣፈጭን አብዝቶ መመግብ የረሃብ ስሜት እንዲሰማን እንዲሁም በብዛት እንድንመገብም ያደርጋል
ስለዚህ የሰውነት ክብደትዎን ለማስተካከል የሚወስዱትን የስኳር መጠን ቢቀንሱ ይመከራል።
✓ ለጤናማ ጥርስ
ነጭና የሚያንፀባርቁ ጥርሶችን እንዲኖርዎ ከፈለጉ የሚወስዱትን የስኳር መጠን ይቀንሱ። ጣፋጭ የምናዘወትር ከሆነ በአፍ ውስጥ የሚገኙ ባክቴሪያዎች እንዲበራከቱ ስለሚያደርግ ለጥርስ እና ድ ድ ህመም እንድንጋለጥ ያደርጉናል። ለጤናማ ጥርስ ስኳርን ማዘውተር አይመክርም!
✓ ለቆዳ ጥራት
ስኳር ለቆዳችን መሰንጣጠቅ እና ጥራት ማጣት ይዳርጋል። በሴሎች ውስጥ የሚገኘውን ውሃ ስለሚያስወጣ ለቆዳ ድርቀት ይዳርጋናል።
✓ ቋሚ የሆነ ሃይል እንዲኖረን
ስኳር እንደተመገብነው ከፍተኛ የሆነ ሃይልን የሚሰጥ ስለሆነ ንቁ ያደርገናል ነገር ግን ወድያውኑ መጠኑ በሚወርድ ጊዜ የድካምና የመራብ ስሜት እንዲሰማን ምክንያት ይሆናል ስለዚህም ባያዘወትሩ ይመከራል።
✓ ለጤናማ ልብ
ሰውንታችን ያልተጠቀመውን ስኳር ወደ ስብነት ለውጦ የሚያስቀምጥ ሲሆን ይህ የስብ መጠን በሚጨምር ጊዜም ለተለያዩ የልብ ህመሞች እና ለስትሮክ የመጋለጥ እድልዎን ስለሚጨምር ቢጠነቀቁ መልካም ነው።
ጤና ይስጥልኝ
(በዶ/ር ሆነሊያት ኤፍሬም ቱፈር)

Keine Kommentare:

Kommentar veröffentlichen