1- የፈረንጅ እርሾ (baking soda) -የፈረንጅ እርሾ ቀላል እና ብዙ ወጪ የማያስወጣ ነገር ሲሆን ፎሮፎር እና የሚያሳክኩ ነገሮችንም ያጠፋልናል፡፡ እርሾውን በመበጥበጥ በደረቅ ጸጉር ላይ ይቀቡት የጭንቅላትዎ ቆዳን መንካቱን ያረጋግጡ፡፡ ከዛም በሻምፖ በማሸት ይታጠቡ፡፡
2- አቡካዶ - አቡካዶ የጭንቅላታችን ቆዳ በማለስለስ ፎሮፎር ተመልሶ እንዳይዘን ያደርጋሉ፡፡ ፀጉርዎን ከመታጠብዎ በፊት አንድ አቡካዶ በመቀባት ጭንቅላትዎን ይሹት፡፡ ከ20 ደቂቃ በኋላ በሙቅ ውሀ ይታጠቡት፡፡ ከዛም ጸጉርዎ ጠንካራ እና ወዛም ሲሆን ጭንቅላቶ ደግሞ ከፎሮፎር ነፃ ይሆናል፡፡
...
3- የሎሚ ጭማቂ -በሻምፖ ፀጉርዎን ከታጠቡ በኋላ በሎሚ ጭማቂ ይታጠቡት፡፡ ይሄም ሻምፖ የሚያፀዳውን ፎሮፎር በማስወገድ ያፀዳልናል፡፡ የሎሚ ጭማቂ በተጨማሪም የፀጉርዎን ቀለም ለማድመቅ ይረዳዎታል፡፡
4- ማር- ማር ኢንፊክሽን እና የጭንቅላት ፈንገሶችን ለማጽዳት ጠቀሜታ አለው፡፡ ማሩን በትንሹ በማሞቅ ትንሽ የሎሚ ጭማቂ በመጨመር ፀጉርን መቀባት ቆዳን በደንብ አድርጎ ያፀዳል፡፡ ከዛም ለ 10 ደቂቃ በማቆየት በሙቅ ውሀ እና በኮንዲሽነር መታጠብ ይቻላል፡፡
5- የኮኮናት ዘይት - የኮኮናት ዘይት ለፎርፎር እና ለደረቅ የጭንቅላት ቆዳ ፍቱን መዳኒት ነው በተጨማሪም ፀጉራችን በፍጥነት እንዲያድግ ይረዳናል፡፡ በሻምፖ ፀጉርዎን ከታጠቡ በኋላ የኮኮናት ዘይቱን ሞቅ በማድረግ ጭንቅላትዎን እና ፀጉርዎን በማዳረስ ከተቀቡ በኋላ ለአንድ ሰአት ያህል በላስቲክ ይሸፍኑት ከዛም በቀዝቃዛ ውሀ እና ኮንዲሽነር ይታጠቡ፡፡by,Selamall Online Information Depot
ጤና ይስጥልኝ
ለወዳጅዎ ያካፍሉ Share

Keine Kommentare:
Kommentar veröffentlichen